በአፍሪካ ሰላም ፣ ጸጥታ እና መረጋጋትን ዙሪያ የአፍሪካ ህብረት ባዘጋጅው ስብሰባ ላይ የኳታር መንግስት ተሳተፈ

በአፍሪካ ሰላም ፣ ጸጥታ እና መረጋጋትን ለማጠናከር ሲባል በቪድዮ ኮንፈረስ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ቡድን የአስራ አንደኛው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ኳታር ተሳተፈች፡፡

ስብሰባው “በአፍሪካ የሽምግልና የወደፊት እጣፈንታ ... የመሳሪያ ድምፅ እንዳይሰማ ስለ ማድረግ እና ከ (ኮቪ -19) የተገኙትን ትምህርቶች” ዙሪያ ተወያይቷል ፡፡

በኢፌዴሪ የኳታር አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ የሆኑት ክቡር አምባሳደር ሚስተር ሀማድ ቢን መሀመድ አል ዶሳር የኳታርን መንግስት በመወከል በውይይቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡