የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በ 1958 በአፍሪካ ሀገራት አባላት መካከል ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጎልበት የተቋቋመ ሲሆን ከአምስት የ ECOSOC ቀጠናዊ ኮሚሽኖች ውስጥ አንዱ ነው። ኮሚሽኑ በሚከተሉት ቁልፍ ዘርፎች ላይ ያተኮረ ነው፦
- ማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲና አስተዳደር
- ክልላዊ ውህደት እና ንግድ
- የግሉ ሴክተር ልማት እና ፋይናንስ
- መረጃ እና ስታቲስቲክስ
- ቴክኖሎጂ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ
- ·• ሥርዓተ-ጾታ፣ ድህነት እና ማህበራዊ ፖሊሲ
- ·• የኢኮኖሚ ልማት እና ዕቅድ
እንዲሁም ሌሎች አምስት የክልል ጽ/ቤቶች አሉ (SROs):
- ሰሜን አፍሪካ (ሞሮኮ)
- ምዕራብ አፍሪካ (ኒጀር)
- መካከለኛው አፍሪካ (ካሜሩን)
- ምስራቅ አፍሪካ (ሩዋንዳ)
ደቡብ አፍሪካ (ዛምቢያ)