አፍሪካ ህብረት


እ.ኤ.አ. በ1963፣ 32 ነፃ መንግስታት የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ያቋቋሙ ሲሆን እ.ኤ.አ. በ 2002 የአፍሪካ ህብረት ከተቋቋመ በኋላ የአባላቱ ቁጥር ወደ 45 ደርሶ ነበር። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ራዕይ የነበረው ባለፈው ግማሽ ምዕተ ዓመት አህጉሪቱ እየገጠሟት የነበሩትን ተግዳሮቶች እንዲሁም የቅኝ ግዛት እና የዘር መድልዎ መወገድን በተመለከተ ነበር። በ 1990 ዎቹ መገባደጃ ላይ መሪዎች በተለወጠው ዓለም አዳዲስ ተግዳሮቶችን ለመወጣት የድርጅቱን ራዕይ ማስተካከል አስፈላጊ መሆኑን ተወያይተዋል። እ.ኤ.አ በ 2002 በዱርባን ጉባዔ ላይ የአፍሪካ ህብረት መሪዎች እና መንግስታት የመጀመሪያ ጉባዔውን ሲያደርግ ፋውንዴሽን አቋቁሞ፤ አህጉሪቱ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በባህል እና በማህበረሰቡ ውስጥ ግቦቹን ለማሳካት እንደ አላማ በመያዝ ጥረቱን ቀጥሏል። እ.ኤ.አ በ2014 ይፋ በተደረገው የ2063 አጀንዳ አህጉራዊ አንድነት ለመመስረት የሚያስችሉ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን መርሀግብሮች ለይቶ አስቀምጧል።

የኳታር መንግስት እ.ኤ.አ. በ 2014 የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ አባል የሆነች ሲሆን ሊቢያ የሚገኙ አፍሪካዊያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ፣ የፀጥታ እና ማህበራዊ መስኮችላይ ለመተባበር የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከ20 ሚሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ጋር በኳታርና በአፍሪካ ህብረት  መካከል ተፈርሟል።

ለበለጠ መረጃ የአፍሪካ ህብረትን ድረ ገጽ ይጎብኙ፡ www.au.in