ፖለቲካ


በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ ስርዓት ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ሲሆን ፓርላማው ሁለት ሕግ የማውጣት ስልጣን ያላቸው ም/ቤቶች አሉት(የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሪሽን ም/ቤት)። የዳኝነት የበላይ ስልጣን የጠቅላይ የፌዴራል ፍ/ቤት ነው። በአስተዳደራዊ በኩል፣ ሀገሪቷ በአስር ክልሎች የተዋቀረች ሲሆን እንደሚከተለው ተዘርዝሯል፡

  • አፋር
  • አማራ
  • ቤኒሻንጉል
  • ጋምቤላ
  • ሐረር
  • ኦሮሚያ
  • ሲዳማ
  • ሶማሌ
  • ደቡብ ክልል
  • ትግራይ
  • ሁለት ልዩ መስተዳደር ከተሞች

_ አዲስ አበባ

_ ድሬዳዋ

 

ስለ አዲስ አበባ:  አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማና ትልቋ ከተማ ስትሆን ከታሪካዊ ፣ ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታዋ አንጻር የአፍሪካ መዲና ተብላ ትጠራለች ፡፡ እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት መቀመጫ ናት፡፡ ከተማዋ ከባህር ጠለል በግምት 2,400 በላይ ትገኛለች፡፡ ከተማዋ ከደህንነት አንጻር በመጠኑ ሰላማዊ የሚባል ቢሆንም ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡