ጥቅል መረጃዎች


መገኛ

ኳታር በውሀ የተከበበች መሬት ስትሆን በአረብ ሰላጤ ምዕራባዊ ዳርቻ መካከል የምትገኝ ሀገር ናት። ከኳታር ጋር በጣም ትስስር ካላቸው ደሴቶች መካከል ሐሉል፣ ሻሩሕ እና አላልሻት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።

 

የመሬት አቀማመጥ

መሬቱ በዋናነት ጠፍጣፋ አለታማ ሜዳ ያዘለ ሲሆን፤ በምዕራባዊው በያቤል ዱሃንሃን እና በሰሜናዊው ክፍል በበልባ ፉያርት በዝቅተኛ የኖራ ድንጋይ ቁፋሮዎች ተከብቦ ይገኛል። ይህ ሜዳ ብዙውን ጊዜ የተለያዩ የተፈጥሮ እጽዋት መኖሪያ ነው ተብሎ የሚታሰብ ሲሆን በሰሜናዊ እና የመካከለኛ አካባቢዎች ላይ ባሉ (አል-ሪያድ) በመባል በሚጠሩት በርካታ  መሬት ገብ በሆኑ ባህሮች (ኮሮች) ፣ ቦዮችና ሸለቆዎች ይታወቃል።

 

ስፋት

የኳታር ቆዳ ስፋት 11521 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ነው

 

የህዝብ ቁጥር

ኳታር አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ ያህል(በ2012 የህዝብ ቆጠራ መሰረት) ህዝብ የሚኖርባት ሲሆን 83% የሚሆኑት ዶሀ ውስጥ ነው የሚኖሩት። ሌላው ከከተማ ወጣ ያለችው ዋነኛ ከተማ አልረያን ትሰኛለች።

 

ዋና ከተማ

ዶሀ የኳታር ዋና ከተማ ነች

 

ቋንቋ

አረብኛ የሀገሪቱ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ሲሆን አእንግሊዝኛ ሌላው በስፋት አገልግሎት ላይ የሚውል ቋንቋ ነው

 

ሐይማኖት

እስልምና የሀገረ ኳታር ኦፊሴላዊ ሐይማኖት ሲሆን፣ ኢስላማዊ ስነ ህግ(ሸሪዓ) ዋነኛው የህግ ምንጭ ነው።

 

የአየር ንብረት

ኳታር በረሀማ የየአየር ንብረት ያላት ሲሆን ሞቃታማ በጋ፣ ወበቃማ ጸደይ እና አነስ ያለ ዝናብ የሚዘንቡባቸው ጊዜያት አሉ።

 

ዐበይት ከተሞች

ዶሀ፣ አልዋክራህ፣ አልኾር፣ ዱኻን፣ አልሸማል፣ ምሳጂድ፣ ራስላፋን እና ሌሎች።

 

ገንዘብ

የቀጠር ሪያልQa(አንድ ሪያል = 100 ዲርሀም), እና አንድ የአሜሪካ ዶላር = የኳታር ሪያል ቀጠር 3.65 (የፀና/የማይቀያየር መጠን).

 

የሀገረ ኳታር ባንዲራ

የኳታር ብሔራዊ ባንዲራ የወይን ጠጅ ቀለም መደብ ኖሮት ዘጠኝ ሰፋፊ ወደ ወይን ጠጁ የተቅጣጩ መስመሮች አሉት። የባንዲራው ትርጉም እንደሚከተለው ነው፡

  • ነጩ ቀለም የሚወክለው በአለም አቀፍ ደረጃ እንድሚታወቀው ሰላምን ነው.
  • ወይን ጠጅ ቀለሙ፤ ኳታር በተለያዩ አጋጣሚዎች በተለይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛ አጋማሽ ባደረገቻቸው ውጊያዎች የፈሰሰውን ደም ይወክላል።
  • ባለዘጠኝ ጫፍ የተቅጣጫው መስመር በግልጽ የሚያሳየው የኳታር እና የብሪታንያ የ1916 ስምምነት መደረጉን ተከትሎ ኳታር የአረብ ባሕረ ሰላጤ 9 ሀገራት ውስጥ አንዷ አባል መሆኗን ነው። ይህ በኳታር የብሔራዊ ባንዲራ አቀማመጥ እና ቀለምን በተመለከተ በ 1931 በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተመዝግቧል።

 

ኦፊሴላዊ የስራ ሰዓት

  • በሚኒስትርና በመንግስት ቢሮዎች ከጠዋቱ 7፡00 እስከ ከሰዓት 8፡00 ነው።
  • በግል ድርጅቶች ከጠዋቱ 2፡00 እስከ እኩለ ቀን 6፡00፤ እንዲሁም ከከሰዓት 10፡00 እስከ ምሽቱ 2፡00 ነው።
  • አርብና ቅዳሜ በኳታር የሳምንቱ የእረፍት ቀኖች ናቸው።

 

የሰዓት አቆጣጠር

GMT +3 ሰዓታት.

 

Electric Current

240V/50Hz.