የኳታርና ኢትዮጵያ ግንኙነት


በኳታር እና በኢትዮጵያ ፌድራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መካከል ዲፕሎማሳዊ ግንኙነት የተጀመረው እ.ኤ.አ በ 1995 ሲሆን፤ ይህም ተፈፃሚ የሆነው በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት እና በኳታር መካከል ዲፕሎማሳዊ ግንኙነቶች ለማቋቋም የሚያስችል ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ነበር። የሁለቱም አገራት የፖለቲካ እና የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በግልጽ የሚታይ መሻሻል ያሳየው እ.ኤ.አ በ2012 የኳታር ኤምባሲ በአዲስ አበባ የተከፈተ ጊዜ ሲሆን በተለይም ታሪካዊ የክብርነታቸው ሼክ ሐማድ ቢን ኻሊፋ አል-ታኒ እ.ኤ.አ በሚያዝያ ወር 2013 ያደረጉት ጉብኝት እና በተጨማሪ በአሚር ታሚም ቢን ሃማድ አል-ሳኒ የአዲስ አበባ ጉብኝት እና የቀድሞው ጠ/ሚ ሃይለማሪያም ደሳለኝ የኳታር ጉብኝት ይጠቀሳል፡፡ በተጨማሪ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዶሃን በፈረንጆቹ 2019 አፕሪል ወር ጎብኝተዋል ፡፡ የኳታር የኢትዮጵያ ቴክኒክ ኮሚቴ በግብርና፣ በባህል፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን እና በኃይል ዘርፍ በትብብር በጋራ ለመስራት እና ለመወያየት ወቅታዊ ስብሰባዎችን ያካሂዳል ፡፡