የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ለኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የፅሁፍ መልእክት ላኩ

    

የኳታር ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትርና የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ሼኽ ካሊድ ቢን ካሊፋ ቢን አብዱልአዚዝ አል ታኒ ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ አሊ በሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ለመደገፍ እና ለማጠናከር ስለሚቻልበት ሁኔታ የጽሑፍ መልእክት ልከዋል፡፡ መልዕክቱን ያዘለውን ደብዳቤ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ከክቡር ሀማድ ቢን መሐመድ አል ዶሳር የኳታር አምባሳደር ተቀብለዋል።